top of page



የምስካበ ቅዱሳን አርብዓ ሐራ መድኃኔዓለም ማህበር አመሠራረት በአጭሩ።
ማኅበራችን የአርብዓ ሐራ መድኃኔዓለም የተመሠረተው በእኛ ዘመን አቆጣጠር ጥቅምት 27 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲሆን ስያሜው የተገኘው በቅድስት ሀገራችን በሸዋ ክፍለ ሀገር በመንዝና ግሸ አውራጃ ልዩ ስሙ ይገም ወይም ማማ ምድር ከሚገኘው ከታላቁ ከምስካበ ቅዱሳን አርብዓ ሐራ መድኃኔዓለም ገዳም ነው። ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት ከዚያ ገዳም በሚመጣው እምነት የተፈወስን ጥቂት ሰዎች መድኃኔዓለምን በየወሩ ለመዘከርና ለሌሎች ለታመሙና ለተጨነቁ ወገኖቻችን የቸሩ አምላካችን የመድኃኔዓለምን ተአምራትና የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሐራ ድንግልን ተጋድሎ በመመስከር ፈውስና በረከት እንዳሰብነውና እንደተመኘነውም በዳላስ ብቻ ሳንወሰን እምነቱን ከሦስት መቶ በላይ ለሚሆኑ በተለያዩ የአሜሪካ ክፍላተ ሀገር ለሚኖሩ ወገኖቻችን አድለናል።
bottom of page